በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መሥከረም 6/2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።

0
89

 

በታንዛኒያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር በይፋ ተጀምሯል።

ከአዘጋጇ ታንዛኒያ እና ከሩዋንዳ ጋር በምድብ አንድ የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታዋን መሥከረም 7/2019 ዓ.ም የምታከናውን ሲኾን በመክፈቻው ጨዋታ በአዘጋጇ ታንዛኒያ የተሸነፈችውን ሩዋንዳን ትገጥማለች።

የምድብ ጨዋታዎችን በበላይነት የሚያጠናቅቁ ሦሥት ቡድኖች እና አንድ ምርጥ ሁለተኛ የወጣ ቡድን በድምሩ 4 ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ።

ወደ ፍጻሜው የሚያልፉት ሁለቱ ቡድኖች የሴካፋ ዞንን ወክለው በጋና አዘጋጅነት በሚካሄደው የ2027 የካፍ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የመሳተፍ ዕድል ያገኛሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_06_2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here