የ2026/27 የኢሮፓ ሊግ ውድድር ዛሬ በሚካሄዱ ጨዋታዎች ይጀመራል።

0
102

 

ኢሮፓ ሊግ ከቻምፒየንስ ሊጉ ቀጥሎ በየዓመቱ የሚካሄድ ታላቅ የአውሮፓ ክለቦች የውድድር መድረክ ነው።

የዓመቱ የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ባለፈው ሳምንት መጀመሩ የሚታወስ ሲኾን ኢሮፓ ሊግም እንደ ቻምፒዮንስ ሊጉ 36 ክለቦችን በአንድ ምድብ አሰልፎ ዛሬ ምሽት ይጀመራል።

በምሽቱ ከሚካሄዱት 9 ጨዋታዎች መካከል የጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ከፖርቹጋሉ ቤነፊካ የሚገናኙበት ግጥሚያ ይጠበቃል።

ሁለቱ ክለቦች በአውሮፓ የውድድር መድረክም ኾነ በየሀገሮቻቸው ሊጎች የደመቀ የውጤታማነት ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ኤሲ ሚላን በጣሊያን ሴሪያ ኤ 19 ጊዜ ሻምፒዮን ሲኾን የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ደግሞ 7 ጊዜ አንስቷል።

2 ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ የኾነው ቤነፊካ በበኩሉ በፖርቹጋል ሊግ 38 ጊዜ ሻምፒዮን በመኾን ባለክብረወሰን ነው።

ሁለቱ ታላላቅ ክለቦች በዘንድሮው የኢሮፓ ሊግ ውድድር መክፈቻ የሚገናኙበት ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ በሚላን ሜዳ ሳንሲየሮ ስታዲየም ይካሄዳል።

በምሽቱ በሚካሄዱ ሌሎች የኢሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች :-

👉ሰንደርላንድ – ከኤ ዜድ አልክማር

👉አንደርሌክት – ከሊዮን

👉ባየር ሊቨርኩሰን – ከሴልጄ

👉ኦሎምፒያኮስ – ከጃኒዬሎኒያ

👉አራራት – ከስፓርታ ፕራግ

👉ኦሞኒያ – ከሴልታ ቪጎ

👉ስትሩም ግራዝ – ከሬንስ

👉ሀፖል ቢር ሼቫ – ከዳይናሞ ዛግሬቭ ይገናኛሉ።

ባለፈው ዓመት የኢሮፓ ሊግ ውድድር የእንግሊዙ አስቶን ቪላ ሻምፒዮን መኾኑ ይታወሳል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_06_2019_ዓ_ም

በኃይሌ አበራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here