የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛው መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

0
72
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛው መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።
ዛሬ በሚካሄደው የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ላለፉት ስምንት ዓመታት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኾነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኢሳይያስ ጅራ ብቸኛ ዕጩ ኾነው ቀርበዋል። ዕጩ ፕሬዝዳንቱ ኢሳይያስ ጅራ አብረዋቸው የሚሠሩ የሥራ አሥፈጻሚ እና የተጠባባቂ ሥራ አሥፈጻሚ ዕጩ አባላትን ቀደም ብለው ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሠረት ፦
ለሥራ አሥፈጻሚነት የቀረቡ ዕጩዎች፦
👉ዶክተር ዳኛቸው ንግሩ
👉ወይዘሮ ሐቢባ ሲራጅ
👉አቶ አበባው ሰለሞን
👉አቶ አንበሴ አበበ
👉ወይዘሮ ሠርካለም ሳሙኤል
👉ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ
👉ኮሚሽነር አለሙ መግራ
👉አቶ ደመላሽ ይትባረክ
ለተጠባባቂ ሥራ አሥፈጻሚነት የቀረቡ ዕጩዎች፦
👉አቶ ሸረፋ ደሌቾ
👉አቶ ኢብራሂም ሙክታር
👉ወይዘሮ በሀብቷ አስቻለው
👉ዶክተር መሠረት ሙሉጌታ
👉አቶ አብዱልፈታህ መታን ኾነው ቀርበዋል።
በባዘዘው መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here