አሌክሳንደር ዝቬሬቭ ታላቅ የገንዘብ ሽልማት ያለውን ውድድር አሸነፈ፡፡

0
99
ጀርመናዊው አሌክሳንደር ዝቬሬቭ አሜሪካዊውን ቤን ሼልተንን 3 ለ 1 በኾነ ድምር ውጤት በማሸነፍ የዩኤስ ኦፕን የወንዶች ነጠላ ሻምፒዮን ኾኗል።
የ29 ዓመቱ ተጫዋች በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከፈረንሳይ ኦፕን ቀጥሎ ሁለተኛው የግራንድ ስላም ዋንጫው ሲኾን በታሪኩ ደግሞ የመጀመሪያው የዩኤስ ኦፕን ክብር ነው።
ዝቬሬቭ በማሸነፊያ ነጥብ ላይ ጨዋታውን ማሸነፉን ወዲያው ባለማስተዋሉ ለቀጣዩ ሰርቭ ሲዘጋጅ የነበረበት አጋጣሚ የውድድሩ አዝናኝ ገጠመኝ ኾኖ አልፏል።
ኤሌና ሪባኪና የሴቶች የነጠላ ፍፃሜ ውድድር ላይ የሁለት ጊዜ ተከታታይ ሻምፒዮኗን አሪና ሳባሌንካን በማሸነፍ የመጀመሪያዋን የዩኤስ ኦፕን ዋንጫ አንስታለች ::
የውድድሩ አሸናፊዎች ዝቬሬቭ እና ሪባኪና እያንዳንዳቸው ውድ የተባለውን የ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ወይም 880 ሚሊዮን ብር ሽልማትም አግኝተዋል፡፡
በአጠቃላይ በዚህ ውድድር 108 ሚሊዮን ዶላር ለሽልማት ብቻ ወጭ ኾኗል፡፡ ይህም ከቴንስ ውድድሮች ሁሉ ከፍተኛ ሽልማት የወጣበት ያደርገዋል፡፡
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here