ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁበት የዓለም አትሌቲከስ አልቲሜት ሻምፒዮንሺፕ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል።

0
112

 

ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት መካሄድ የጀመረው የዓለም አትሌቲከስ አልቲሜት ሻምፒዮንሺፕ ዛሬ ምሽትም መካሄዱን ይቀጥላል፡፡

በሁለተኛ ቀን ውድድሩ ኢትዮጵያ በሴቶች 1ሺ 500 ሜትር እና 800 ሜትር ፍፃሜ ትካፈላለች።

አስቀድሞ ምሽት 2፡36 ሲል በሚጀምረው የ1ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያ በ4 አትሌቶች ትወከላለች።

ብርቄ ሀየሎም፣ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ሳሮን በርሄ እና ሀረገወይን ካልአዩ ሀገራቸውን ይወክላሉ፡፡

ብርቄ ኃየሎም በርቀቱ በግል የተሻለ እና በዓመቱም ያስመዘገበችው ጥሩ ሰዓት በውድድሩ ለአሸናፊነት እንድትጠበቅ አድርጓታል።

በ5ሺህ ሜትር ዳይመንድ ሊግ የዋንጫ አሸናፊዋ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉም በዚህ ርቀት ኢትዮጵያን ውጤታማ እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡

ከደቂቃዎች በኋላ ቀጥሎ በሚደረገው የ800 ሜትር ውድድር አትሌት ንግሥት ጌታቸው ትወዳደራለች።

3ኛ ደረጃን በማግኘት ወደ ፍፃሜ ያለፈችው አትሌት ንግሥት ጌታቸው በርቀቱ የተሻለ ሰዓት ካላቸው የኬንያ እና አውስትራሊያ አትሌቶች ጋር ትፎካከራለች፡፡

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

ባሕር ዳር #መስከረም_02/2019_ዓ_ም

በሰኢድ ኢብራሂም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here