ሲዳማ ቡና ታሪካዊውን የአህጉር አቀፍ ውድድር ጉዞ ለመቀጠል ዛሬ ከኤጌሎን ጋር ይጫወታል።

0
76

 

ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን በመኾን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው ሲዳማ ቡና፣ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ወሳኝ የኾነውን የመልስ ጨዋታ ዛሬ ያደርጋል።

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ በመጀመሪያው ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ከቻዱ ክለብ ኤጌሎን ጋር ተጫውቶ 0 ለ 0 በኾነ ውጤት መለያየቱ ይታወቃል።

ሲዳማ ቡና ከሜዳው ውጭ ግብ ሳያስተናግድ መመለሱ እና ዛሬ በሀገሩ ሰፊ ድጋፍ የሚያገኝ መኾኑ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን የሰፋ ያደርገዋል።

ጨዋታውም ዛሬ ቀን 10፡00 በበድሬደዋ ስታዲየም ይካሄዳል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_03/2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here