የቼልሲ ፈጣን የግብ ማስቆጠር ጉዞ ይቀጥላል ወይንስ የሃል ሲቲ ግብ መረብ አለመደፈር ይገታል?

0
79

 

በስታምፎርድ ብሪጅ የሚጠበቀው የቼልሲ እና የሃል ሲቲ ፍልሚያ ዛሬ ተጠባቂ ነው።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በስታምፎርድ ብሪጅ የሚደረገው የቼልሲ እና የሃል ሲቲ ጨዋታ በሁለት ተቃራኒ ጠንካራ ብቃቶች የተከበበ በመኾኑ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።

የቼልሲ በዘመኑ ውድድር ባደረጓቸው ሦሥቱም ጨዋታዎች በመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ውስጥ ግብ ማስቆጠር የቻሉበት አስደናቂ የውድድር አጀማመር ላይ ይገኛሉ።

ዘንድሮ ወደ ሊጉ ያደገው ሃል ሲቲ በበኩሉ እስካሁን ምንም ግብ ያልተቆጠረበት የሊጉ ብቸኛው ክለብ በመኾን ድንቅ የሳምንቱ መዝገብ ይዟል።

በዚህ ጨዋታ የቼልሲ ፈጣን የግብ ማስቆጠር ጉዞ ይቀጥላል ወይንስ የሃል ሲቲ ግብ መረብ አለመደፈር ይገታል የሚለው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ጨዋታውም ቀን 11፡00 ላይ ይካሄዳል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

ባሕር ዳር #መስከረም_02/2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here