ፍረወይኒ ኃይሉ፣ አለሽኝ ባወቅ እና አዲሱ ይሁኔ በአልቲሜት ሻምፒዮና ይሳተፋሉ።

0
87

 

የዓለም አትሌቲክስ አልቲማት ሻምፒዮና የመጨረሻ የተሳታፊዎችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ተካትተዋል::

በዓመቱ ውስጥ በነበራቸው ስኬት መሠረት በሴት 3 ውድድሮች በወንድ ደግሞ በ1 ዘርፍ ብቻ አትሌቶች ለሚሊዮን ዶላሩ ድል ይፎካከራሉ።

በዚህም መሠረት በታሪካዊው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮና ላይ አትሌቶቹ በጠንካራ ፉክክር የሚያደርጉ ሲኾን በወንዶች 5ሺህ ሜትር ቢኒያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ሀገራቸውን ወክለው ይሮጣሉ።

በወንዶቹ በዚህ ርቀት ብቻ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን የምንመለከታቸው ይኾናል።

በሴቶች ሦሥት ርቀቶች ላይ ማለትም በ5ሺህ ሜትር ልቅና አምባው፣ አለሽኝ ባወቅ፣ ፋንታየ በላይነህ፣ ሰናይት ጌታቸው፣ ፍረወይኒ ኃይሉ እና ሂሩት መሸሻ ተሰልፈዋል።

በመካከለኛ ርቀት ውድድሮች በኩል በሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ፍረወይኒ ኃይሉ በድጋሚ ድርብ ድል ለማድረግ ትሳተፋለች።

ሳሮን በርሄ፣ ብርቄ ኃየሎም እና ሀረገወይን ካላዩ በዚህ ርቀት ከፍረወይኒ ጋር ቡዳፔስት ላይ ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

እንዲሁም በሴቶች 800 ሜትር ንግስት ጌታቸው ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ተወካይ ኾና በውድድሩ ላይ ትካፈላለች።

ከሁለት ቀናት በኋላ በሀንጋሪ ቡዳፔስት ትኩረት ባገኘው በዚህ መድረክ ከ65 ሀገራት የተወጣጡ 381 ጠንካራ አትሌቶች የሚካፈሉ ይኾናል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ጳጉሜን_02_2018_ዓ_ም

በሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here