2018 የቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜን ካስታወስን ሎሪስ ካሪየስን ማስታወሳችን አይቀርም።
ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ ባደረጉት የፍፃሜ ጨዋታ የግብ ጠባቂው ሁለት ከባድ ስህተቶች ቡድኑ በሪያል ማድሪድ 3ለ1 አንዲሸነፍ ምክንያት ኾነ።
በበርካቶችም ከዚህ በኋላ ወደ ትልቅ ደረጃ እንድማይደርስ ታመነበት።
ከዚያ በኋላ ወደ ተለያዩ ክለቦች ተዘዋወረ። ራሱን ፈልጎ ለማግኘት ባደረገው ጥረትም 2026 ላይ ካሪየስ እንደገና መድረኩ ላይ ተመለሰ።
ሻልክ ከባየርን ሙኒክ ባደረጉት ጨዋታ ሙኒክን ግብ ከማስቆጠር አግዶ ጨዋታውን 0ለ0 እንዲጠናቀቅ አደረገ።
ከሁሉም በላይ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የሃሪ ኬንን ሙከራ በአስደናቂ ብቃት አዳነበት።
ይህ ሰው ከ2018 የቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጀምሮ ስሙ ከስህተት ጋር ተያይዞ ነበር።
በመላ ሊቨርፑላዊያን የተወገዘው ካሪየስ አሁን የጽናት ተምሳሌት ተደርጎ ውዳሴ እየተቸረው ይገኛል።
አሁን መልዕክቱ አንድ ነው። “ውድቀት የስኬት መሠረት ነው!”
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጳጉሜን_03_2018_ዓ_ም
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



