ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የዳያመንድ ሊግ ውድድር በቤልጅየም ብራሰልስ የውድድር ዓመቱ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
በ32 የውድድር ዓይነቶች በሠበሠቡት ነጥብ መሠረት ለፍፃሜ የደረሱ አትሌቶች የዲያመንድ ፈርጡን ለመሸለም ዛሬ እና ነገ ብርቱ ፉክክርን ያደርጋሉ፡፡
ዛሬ 16ቱ የውድድር ዓይነቶች የፍፃሜ ውድድር ሲደረግባቸው ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለት ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡ በተለይ በ5ሺህ ሜትር ሴቶች ስድስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለአሸናፊነት ግምትን አግኝተው ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል፡፡
አጠቃላይ በዚህ ርቀት ከሚሳተፉት 12 አትሌቶች ግማሹን ቁጥር የያዙትም ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ መዲና ኢሳ ከሚሳተፉት አትሌቶች ሁሉ የተሻለ ሰዓት ያስመዘገበች አትሌት ናት፡፡
ልቅና አምባው፣ ፍሬወይኒ ኀይሉ፣ ሰናይት ጌታቸው እና ማርታ አለማሁ በፉክክሩ የሚጠበቁ አትሌቶች ናቸው፡፡ በዚህ ርቀት እንደከዚህ ቀደሙ ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት አትሌቶች በምሽቱ ውድድር ላይ አይካፈሉም፡፡
በሴቶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል አንድ ኢትዮጵያዊት አትሌት ብቻ ትሳተፋለች፡፡ ቀና ቱፋ ከኬንያዊያን እና አሜሪካዊያን አትሌቶች ጋር ፉክክር ታደርጋለች፡፡
በየርቀቱ አንደኛ በመውጣት የሚያሸንፉ አትሌቶች 30 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እና የዲያመንድ ፈርጥ ይሸለማሉ ሲል የዓለም አትሌቲክስ ዘገባ አመላክቷል፡፡
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



