ሊቨርፑል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርገው ትግል ዛሬ ይሳካለት ይኾን?

0
110
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሦሥተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሲጀምር አዲስ አዳጊው ኢፕስዊች ታውን ሊቨርፑልን ይጋብዛል። በአዲሱ አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ እየተመራ ሊቨርፑል በሊጉ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቅቋል።
ሊቨርፑል ዛሬ ከአንድ ዓመት የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰውን ኢፕስዊች ታውንን ማሸነፍ ይጠበቅበታል፤ ከተፎካካሪዎቹ ላለመራቅ። ኢፕስዊች በውድድር ዓመቱ አንድ ጨዋታ ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፎ ዓመቱን ጀምሯል።
ዛሬ በሜዳው ፖርትማን ሮድ የሚያደርገውን ጨዋታ ከቀዮቹ ላይ ሦሥት ነጥብ ለመውሰድ ይታገላል። በዛሬው ጨዋታ በሊቨርፑል በኩል ተከላካዩ ጆ ጎሜዝ እና የፊት መስመር ተጫዋቹ ፌድሪኮ ኬሳ ከጉዳታቸው በማገገማቸው ከሥብሥቡ ውጭ ናቸው።
አዲስ ፈራሚው ብራድሊ ባርኮላ የጨዋታ ዕድል ይሰጠዋል የሚል ተስፋ እንዳለ ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል። ሊቨርፑል ኢፕስዊች ታውንን በራሳቸው ሜዳ ገጥሞ ምንም ጨዋታ አልተሸነፈም ዛሬም ምሽት 4፡00 ላይ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ይጫዎታል።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here