ፊፋ የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበርን በሥም አጥፊነት ከሰሰ።

0
89
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበርን በፕሬዝዳንቱ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ላይ “የሥም ማጥፋት ዘመቻ” እያካሄደ ነው ሲል ከስሷል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር በኢንፋንቲኖ ላይ በስዊዘርላንድ ፍርድ ቤቶች “የገንዘብ ምዝበራ እና ወንጀል ነክ የአመራር ብልሽት” ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀ መኾኑን ገልጿል።
ለዚህም ማስረጃዎችን ለማሠባሠብ በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የሰነድ ይፋ የማድረግ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ፊፋ በአሜሪካ ፍርድ ቤት ባስገባው ምላሽ የፍርድ ቤት ማመልከቻዎች ከስም ማጥፋት ዘመቻ የተለዩ አይደሉም ሲል አጣጥሏል።
በሁለቱ ተቋማት መካከል ይህ ከፍተኛ አለመግባባት የተፈጠረው ፊፋ የዓለም ዋንጫን የንግድ መብቶች ድርሻ (20 በመቶ) ለግል ባለሀብቶች በ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ለመሸጥ አቅዶት በነበረው እና በኋላ ላይ በከፍተኛ ተቃውሞ በሰረዘው ዕቅድ ምክንያት ነው።
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here