10 ሚሊዮን ዶላሩን እና የዲያመንድ ሽልማቱን ማን ይወስዳል?

0
105
የ2026 ዋንዳ ዲያመንድ ሊግ ነገ እና ቅዳሜ ምሽት በሚደረጉ የመጨረሻ ውድድሮች ፍፃሜ ያገኛል።
15ኛ የውድድሩ አስተናጋጅ ከተማ በኾነችው የቤልጂየም መዲና ብራሰልስ የአትሌቲክሱ ኮከቦች ለትልቁ ሽልማት ተፋጥጠዋል።
በ5 ርቀቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እስካሁን በሠበሠቡት ነጥብ በፍፃሜው ለሽልማቱ ከሚጠበቁት መካከል ናቸው።
በሴቶቹ ዘርፍ በ800 ሜትር ሰይዳ ፀሐዬ እና በ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኬና ቱፋ በብቸኝነት ይሮጣሉ።
ፅጌ ዱጉማ እና ብርቄ ሃየሎም በ1ሺህ 500 እና ልቅና አምባው፣ መዲና ኢሳ፣ ፍረወይኒ ኃይሉ በ5ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድርም ኢትዮጵያውያኑ በርከት ብለው የሚፎካከሩበት ርቀት ነው።
በወንዶቹ 3ሺህ ሜትር መሰናክል ሞሮኳዊውን ብርቱ አትሌት ሱፊያን ኤልባካሊ ለመገዳደር ሳሙኤል ፍሬው እና ገመቹ ጎዳና በርቀቱ ተሳታፊ ናቸው።
እንደ ወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ የአሜሪካ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ እና ኔዘርላንድስ አትሌቶች ዳጎስ ካለው ሽልማት ለመጋራት ደርሰዋል።
✍️በአማኑኤል ፀጋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here