ዛሬ በሚጠናቀቀው የዝውውር ወቅት የትኞቹ ዝውውሮች ይጠበቃሉ ?

0
158
የእንግሊዝ የክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡
ክለቦች ራሳቸውን ለማጠናከር ተጫዋቾችን ሲለቁ እና ሲያመጡ የቆዩበት የዝውውር ጊዜ ዛሬ ምሽት 5፡00 ላይ ይበቃል፡፡
እናም እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ይጠናቀቃሉ ተብለው የሚጠበቁ ታላላቅ ዝውውሮችም አሉ፡፡
የቸልሲው አማካይ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ የሚያደርገው ዝውውር በትልቁ ከሚጠበቁት መካከል ነው፡፡
ሲቲ ወሳኙን አማካይ ሮድሪን ለመተካት ያሰበው በ25 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ፈርናንዴዝ ነው፡፡ 120 ሚሊዮን ፓወንድ ያህል በመክፈል ሲቲ ተጫዋቹን የግሉ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ የኤቨርተኑን የመስመር አጥቂ ኢሊማን ኒዲየን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
ሲቲ 60 ሚሊዮን ፓወንድ ለሴኔጋላዊው ተጫዋች እንደሚያወጣ ተዘግቧል፡፡ በምላሹም ሲቲ ወደ ክለቡ ተመልሶ የነበረውን ጃክ ግሪሊሽ በድጋሚ በውሰት ለኤቨርተን የሚሰጥ ይኾናል፡፡
ቸልሲ በአበረታች መድኃኒት ምክንያት ቅጣት ላይ የቆየውን ማይክሎ ሙድሪክን ወደ ቶተንሃም እንደሚለቀው ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል ቸልሲ ግብ ጠባቂውን ሮበርት ሳንቸዝን ወደ ጣሊያኑ ኮሞ በውሰት ወይም በቋሚ ውል ይልከዋል ሲሉ ቢቢሲ እና ስካይ ስፖርትስ አስነብበዋል፡፡
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here