የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከነሀሴ 10-17/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ማካሄዱ ይታወቃል።
በዚህ ውድድር ላይ ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተው የፍጻሜ ተፋላሚ ሆነው 1ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አርሲ ዞን ቮሊቦል ክለብና 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የአዴት ከተማ ቮሊቦል ክለብ ወደ ከተማቸው ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው።
በደጋፊ ህበረ ዜማ ታጅቦ የውድድሩ ድምቀት በመሆን 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የአዴት ከተማ ቮሊቦል ክለብ የክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በተለያየ የእርከን ደረጃ በሚገኙ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
እሁድ በደማቅ የመዝጊያ ፕሮግራም ፍጻሜውን ባገኘው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና አርሲ ዞን፣ አዴት ከተማ እና ስኬት ባንክ ወደ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል ሲል የኢትዮጵያ ቮሊቮል ፌዴሬሽን መረጃውን አጋርቶናል።
መለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



