በ2ኛው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ቮሊቦል ሻምፒዮና አራተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ አዴት ኮዬ ፈቸን 3ለ2 ረቷል ።

0
9
በ6 ክለቦች መካከል ወደ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ በሚደረገው ፉክክር የአማራ ክልል ተወካዩ አዴት ቮሊቮል ክለብ አራት ጨዋታዎችን አድርጎ ሁሉንም አሸንፏል።
11 ነጥብ በማስመዝገብ በመሪነት ተቀምጧል። ለሻምፒዬንነት እድሉን ያሰፋ ሲሆን የቀጣይ አመት ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊነቱን አረጋግጧል።
ተከታዩ አርሲ በስኬት ባንክ 3ለ2 የተሸነፈ ሲሆን ከአዴት በ 2 ነጥብ አንሶ 2ኛ ነው።
ሻምፒዮኑን ለመለየት አዴት ከአርሲ የመጨረሻ ጨዋታቸውን በቀጣይ ያደርጋሉ።
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here