የፈረንሳይ ሊግ 1 የውድድር አመት ከነገ ጀምሮ በሚደረጉ ጨዋታዎች አመቱን ይጀምራል።
ሻምፒዬኑ ፓሪሴን ዥርመ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን እሁድ በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ ሬንስን በማስተናገድ ሊጀምር መርሀግብር ወጥቶለታል። ነገር ግን የሊግ 1 አመራሮች ባደረጉት የሜዳ ግምገማ ፓርክ ደ ፕሪንስ በመበላሸቱ ጨዋታ አይደረግበትም ብለዋል።
ሜዳውና ሳሩ በፈረንሳይ የሀምሌ ወር ሙቀት መጨመር ምክንያት እንደተበላሸ ታውቋል። የሊጉ አመራሮችም ሜዳው ለጨዋታና ለተጨዋቾች ደህንነት ምቹ አይደለም በሚል በተጋጣሚው ሬንስ ሜዳ የእሁዱ ጨዋታ ይደረጋል።
ክለቡ ለቀጣይ መርሀግብሮች የመጫወቻ ሜዳውን ሳር ቀይሮ እንደሚቀርብ ሲገልፅ ነሀሴ መጨረሻ ለሚያደርገው የሞናኮ ፍልሚያ እንደሚደርስም ጠቁሟል።
በሀምሌ ወር በፓሪስ ሙቀቱ በተደጋጋሚ 41 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መድረሱ ይታወሳል።



