ለ22 ዓመቱ ተጫዋች ዩናይትድ 60 ሚሊዮን ፓውንድ ከ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ፓውንድ (add-ons) ያቀረበ ቢሆንም፣ ብራይተን ከዚህ ከፍ ያለ ዋጋ እንደሚሻ ይገመታል።
ባሌባ በአሁኑ ወቅት በቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ከሜዳ የራቀ ቢሆንም፣ ጉዳቱ ለረጅም ጊዜ የሚያቆየው አሳሳቢ ችግር አይደለም።
ዩናይትድ በዚህ ክረምት ዩሪ ቲሌማንስን እና አንድሬ ሳንቶስን ያስፈረመ ሲሆን፣ የካርሎ ባሌባ ዝውውር ከተሳካ ከኮቢ ማይኑ እና ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ጋር በመሆን በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር የአማካይ ክፍሉን የበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላል።
ባሌባ ከፈረንሳዩ ሊል ክለብ በ2023 ወደ ብራይተን ከተቀላቀለ ወዲህ በድምሩ 112 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ ሁለቱም ክለቦች ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁን የሚፈጸም የሚመስል ውይይቶችን እያደረጉ ይገኛሉ።



