አዴት ቮሊቦል ክለብ ፕሪሚየር ሊጉን ሊቀላቀል ተቃርቧል።

0
9
በ2ኛው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ቮሊቦል ሻምፒዮና ሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ አዴት ነብሮን 3ለ0 ረቷል ።
በ6 ክለቦች መካከል ወደ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊጉ ለማደግ በሚደረገው ፉክክር የአማራ ክልል ተወካዩ አዴት ቮሊቮል ክለብ ሶስት ጨዋታዎችን አድርጎ ሁሉንም አሸንፏል።
አዴት ባለፉት ጨዋታዎቹ ስኬት ባንክ እና ለገጣፎን በተመሳሳይ 3ለ0 መርታታቸው ይታወሳል።
የዛሬ ተጋጣሚው ነብሮ 3ቱንም ጨዋታዎች ተሸንፏል።
ኮዬ ፈቸ ከ ስኬት ባንክ እና ለገጣፎ ከ አርሲ የ3ኛ ዙር ጨዋታዎች በመደረግ ላይ ናቸው።
በሻምፒዮናው ከአንደኛ እሰከ ሦሥተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች በ2019 በወንዶች ቮሊቦል ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ይሆናሉ።
አዴት የዛሬ ጨዋታዎችን ውጤት ጠብቆ አልያም በቀጣይ ከቀሩት ሁለት መርሀግብሮች አንዱን ማሸነፍ ያለ ቅድመ ሁኔታ ፕሪሚየር ሊግ መግባት ያስችለዋል።
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here