የእግር ኳስ ቫይታሚን እና በኢትዮጵያ የተረሳው ስራ ስካውቲንግ

0
7
ስካውቲንግ የእግር ኳስ ተጫዋቾችን በመመልከት ችሎታቸውን ፣ጥንካሬ እና አቅማቸውን መገምገም እንዲሁም መረጃ መሰብሰብ ነው።
በዘመናዊ እግር ኳስ አንድ ክለብ አዲስ ተጨዋች ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል መልማዩችን ይልካል። መልማዮችም የተጫዋቹን ፍጥነት፤ ያለውን ችሎታ፤የኳስ ቁጥጥር፤ ውሳኔ አሰጣጥ እና የወደፊት አቅም ይመረምራሉ፡፡ ለክለቡ ያለውን አስፈላጊነት ደረጃ የምክረ ሀሳብ ውሳኔም ይሰጣሉ።
በእኛ ሀገር ተሞክሮ በፕሪሚየር ሊጉ እንኳ ብንወስድ የተጫዋቾችን መረጃ ለመውሰድ ሊግ ካምፓኒው ሊጉን ከመራበት ጊዜ ጀምሮ መጠነኛ መሻሻሎች አሉ።
ነገር ግን አሁንም የተጫዋቾችን ሙሉ መረጃ ለማግኝት ቀላል አይደለም።
በተለያዩ የሊግ እርከኖች ላይ የሚሳተፉ በርካታ ክለቦች ቢኖሩም በረዥም ጊዜ እቅድ ስለማይመሩ ለእነርሱ የጨዋታ ዘይቤ የሚመች ተጫዋች የመመልመል አሰራር ክፍተት መኖሩን የካፍ ኢንስትራክተር እና አሰልጣኝ መብራቱ ሀብቱ ለአሚኮ ገልጿል።
የኢትዩጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህንን አስፈላጊ እና የእግር ኳስ እድገት መሠረት የሆነ ዘርፍ ትኩረት መስጠት አለበት ሲል ሀሳቡንም አጋርቷል።
ፌዴሬሽኑ እንደ ክለብ ላይሰንሲንግ ሁሉ መልማዮችን የሚያበረታታ አሰራር ግዴታን በክለቦች በኩል መፍጠር አለበት የሚለው ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱ ይህ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው ተጫዋች መመልመል ቀላል እንደሚሆን ያስረዳል፡፡
ዳናይት ሲሳይ
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here