በስድስት ክለቦች መካከል በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ዛሬ በጀመረው ውድድር ላይ በአማራ ሊግ ምዕራብ ቀጣና የቮሊቦል ውድድር አሸናፊ የነበረው አዴት ለገጣፎን ገጥሞ 3ለ0 በማሸነፍ አጀማመሩን አሳምሯል።
ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር ላይ ሦሥት የክልል ክለቦች እና አንድ የተቋም ክለብ እየተሳተፉ ነው።
በሻምፒዮናው ከአንደኛ እሰከ ሦሥተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች በ2019 በወንዶች ቮሊቦል ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ይኾናሉ።
ውድድሩ እስከ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



