ቪኒሽየስ ጁኒዬር በቤርናባው ለመቆየት ወስኗል።

0
68
የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተሰላፊ ብራዚላዊው ቪኒሺየስ ጁኒየር ከክለቡ ሪያል ማድሪድ ጋር በውል ማራዘም የተነሳ ውዝግብ ውስጥ መቆየቱ ይታወሳል።
ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ከኾነ ቪኒሺየስ ጁኒየር ዛሬ ከማድሪድ የበላይ አካላት ጋር ወሳኝ ውይይት ካደረገ በኋላ በሪያል ማድሪድ ለመቆየት ወስኗል።
በሪያል ማድሪድ እና በቪኒሽየስ ጁኒየር መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር አሁን ላይ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱም ተነግሯል። ተጫዋቹ እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 2029 ወይም 2030 የሚያቆየውን ውል እንደሚፈራረምም ይጠበቃል።
ተጫዋቹም “እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ እዚህ መቆየት እና ታሪክ መሥራት እፈልጋለሁ” በማለት ለክለቡ ያለውን ታማኝነት በድጋሚ ማረጋገጡ ተነግሯል።
ማድሪድ በዓመት 22 ሚሊዮን ዩሮ የተጣራ ደመወዝ ማቅረቡን ተከትሎ የደመወዝ መዋቅሩን፣ የውል ማፍረሻውን እና የጥቅማጥቅም ጉዳዮችን ለማስተካከል የመጨረሻ ንግግሮች እየተደረጉ መኾኑም ተመላክቷል።
አርሰናል ለተጫዋቹ በዓመት 30 ሚሊዮን ዩሮ ደመወዝ ለመክፈል ፍላጎት አሳይቶ የነበረ ቢኾንም የቪኒሺየስ ምርጫ ማድሪድ በመኾኑ ዝውውሩ የመሳካት ዕድሉ አነስተኛ መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቪኒሺየስ ከዓለም ዋንጫ እረፍት መልስ ከአዲሱ አሠልጣኝ ሆሴ ሞውሪንሆ ጋር ልምምድ የጀመረ ሲኾን አሠልጣኝ ጆዜም ሁልጊዜ ደስተኛ እና ራስህን ኾነህ እግር ኳስን ተጫወት የሚል ምክር እንደሰጡት ራሱ ቪኒሽየስ ተናግሯል።
በአድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here