አሰፈሪ ኾኖ የመጣው ሪያል ማድሪድ።

0
62

 

የሪያል ማድሪድ የማጥቃት መስመር ለ2026/27 የውድድር ዘመን እጅግ አስፈሪ ገጽታ ተላብሶ መጥቷል።

የያንን ዲዮማንዴ ዝውውር ይፋ መኾንን ተከተሎ የሪያል ማድሪድ የማጥቃት አማራጮች ለ2026/27 የውድድር ዘመን እጅግ አስፈሪ ገጽታን ይዞ ብቅ ብሏል።

በአሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የሚመራው የሎስ ብላንኮሱ ሥብሥብ እንደ ቪኒሲየስ ጁኒየር፣ ጁድ ቤሊንግሃም፣ ኪሊያን ምባፔ እና አዲሱ ፈራሚ ያን ዲዮማንዴ ያሉ ዓለም አቀፍ ኮከቦችን በአንድ ላይ ማሰለፍ የሚያስችለው ሰፊ ሥብሥብ በእጁ አስገብቷል።

እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ይህ በከፍተኛ ፍጥነት፣ በፈጠራ ብቃት እና በግብ ማስቆጠር ክህሎት የተገነባው የማጥቃት መስመር በላሊጋውም ኾነ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ለተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች እረፍት የሚነሳ ትልቅ ስጋት እንደሚኾን ከወዲሁ ይጠበቃል።

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_01_2018_ዓ_ም

✍️በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here