ዶሚኒክ ሶቦስላይ እስከ ሰኔ 2031 ድረስ የሚቆይ አዲስ ኮንትራት ከሊቨርፑል ጋር ተፈራርሟል።
ተጫዎቹ አሁን ላይ በክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከኾኑት ተጫዋቾች ተርታ መሰለፉን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ዘግቧል።
ዶሚኒክ ሶቦስላይ ለክለቡ የወደፊት ጉዞ ቁልፍ ተጫዋች ተደርጎ ይወሰዳል። ሊቨርፑል የተጫዎቹን ውል ማራዘሙን ይፋዊ መግለጫ በቅርቡ እንደሚያወጣም ተገልጿል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_10_2018_ዓ_ም
በያየህ ፈንቴ



