🌏 በ2026 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ፖርቹጋል ከስፔን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ በጉጉት ይጠበቃል። ፖርቹጋል በ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ክሮሺያን 2 ለ 1 በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀሏ ይታወሳል።
በአሠልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የምትመራው ፖርቹጋል ወደ ሩብ ፍጻሜው ለመግባት በምታደርገው ጉዞ ከስፔን ትልቅ ፈተና እንደሚገጥማት ይጠበቃል።
🌏 የዓለም ድንቁ ተጫዎች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2026ቱ የዓለም ዋንጫው የመጨረሻው እንደሚኾን አስታውቋል። የእግር ኳስ ባለውለታ፤ የጥንካሬ ተምሳሌት፤ የጥረት አርዓያ እንደኾነ በዓለም ዘንድ የተመሰከረለት ነው።
ሮናልዶ እና ብሔራዊ ቡድኑ ስፔንን እና ቀጣዩን ዙሮች አሸንፎ ዋንጫውን ያነሳ ይኾን ወይንስ በስፔን ተሸንፎ የዘመናት ሕልሙ የኾነውን የዓለም ዋንጫ ሳያሳካ ተሳትፎውን ያጠናቀቅ ይኾን? የሚለው በጉጉት ይጠበቃል።
በ2018 ዓለም ዋንጫ ውድድር ከስፔን ጋር በነበረው ጨዋታ ሃትሪክ መሥራት ችሎ እንደነበር ይታወሳል። በ41 ዓመቱ በዓለም ዋንጫው እየተሳተፈ የሚገኘው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዛሬን ከእስፔን ጋር ያን መድገም ይችል ይኾን? የሚለው ተጠባቂ ነው።
በዘንድሮ 🌏 የዓለም ዋንጫ 3 ግቦችን አስቆጥሯል።
ያማልን እና ሌሎች ክዋክብቶችን የያዘችው ስፔን ከ
ለፖርቹጋል ትልቅ ፈተና እንደምትኾንባት ይጠበቃል።
ሰፔን በ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኦስትሪያን በመርታት 16ቱን መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡ የ2010 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ስፔን በድጋሚ በመድረኩ ለመንገስ የምታደርገውን ጉዞ ለማጠናከር የምታደርገው ትግል ነው።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል።
በሌላ የዓለም ዋንጫ መርሐ ግብር ሌሊት 9:00 ላይ አሜሪካ ከቤልጀም ይጫወታሉ።
#አሚኮ_ዜና#ስፖርት
#ባሕር_ዳር#ሰኔ29_2018ዓ_ም
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ



