ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም
ንጋት አካባቢ በተካሄደው 🌎የ 2026 የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሜክሲኮ ኢኳዶርን 2 ለ 0 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች።
ለሜክሲኮ ⚽️ጁሊያን ኩይኖኔስ በ22ኛው ደቂቃ እና ⚽️ ራውል ጄሚኔዝ በ31ኛው ደቂቃ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በጨዋታው 95ኛ ደቂቃ ላይ የኢኳዶሩ ተጫዋች ፒዬሮ ሂንካፔ አፍን ይዞ ማናገር በሚለው የፊፋ ሕግ መሠረት በሠራው ጥፋት በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።
በዚህ ውጤት መሠረትም ኢኳዶር ከትልቁ የዓለም ዋንጫ መድረክ ተሰናብታለች።
#አሚኮ ዜና#🌏ዓለም ዋንጫ#⚽️ስፖርት
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።



