ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም የስፔን ላሊጋ የ2026/27 የውድድር ዘመን መርሐ ግብር ይፋ ኾኗል።
የላሊጋው የውድድር ዘመን በነሐሴ አጋማሽ ላይ እንደሚጀምር እና በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተጠቅሷል።
እንደ ቢ ሶከር ዘገባ በሊጉ⚽️በመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር :-
– ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ
– ባርሴሎና ከ አትሌቲክ ቢልባኦ
– አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ማላጋ ጋር ይጫወታሉ።
የመጀመሪያው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ በአስረኛ ሳምንት መርሐግብር ካምፕ ኑ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።
የመጀመሪያው የማድሪድ ደርቢ በሊጉ ሰባተኛ ሳምንት መርሐግብር ላይ እንደሚደረግ ቢ ሶከር አስነብቧል።
#አሚኮ_ዜና⚽️#ስፔን_ላሊጋ #ሰፖርት
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



