ኮትዲቫር ከኖርዌይ፤ ፈረንሳይ ከስዊድን የሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጠበቃል።

0
4

 

ባሕር_ዳር: ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
ኮትዲቫር ከኖርዌይ ምሽት 2፡00 ላይ ከሚደረጉ ጨዋታዎች ውስጥ አንዱ ነው። አፍሪካውያኑ ዝኾኖች በአካላዊ ብቃት እና በፍጥነት የታገዘውን አጨዋወታቸውን ይዘው ወደ ሜዳ በመግባት ለኖርዌይ የአየር ላይ ኳሶች መሀንዲሶች ፈተና እንደሚኾኑ ነው የሚጠበቀው።

ኖርዌይ ከመልሶ ማጥቃት የምታገኛቸውን ዕድሎች ለመጠቀም ስትሞክር ኮትዲቫር ደግሞ የመሀል ሜዳ የበላይነትን ለመውሰድ እንደሚጫወቱ ከምድብ ጨዋታቸው በመነሳት መረዳት ይቻላል።

የኮትዲቫሩ ሴኮ ፎፋና እና ፍራንክ ኬሲዬ የመሃል ሜዳውን ጉልበት እና ፍሰት በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚወስዱ ነው የሚጠበቀው።

ሲሞን አዲንግራ በክንፍ መስመር ላይ ባለው አስደናቂ ፍጥነት እና ክህሎት የኖርዌይን ተከላካዮች ለማስጨነቅ ቁልፍ ተጫዋች እንደሚኾን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

በኖርዌይ በኩል በድንገት የግብ ዕድል መፍጠር የሚችለው አርሊንግ ሃላንድ የማጥቃት አጨዋወቱ ለኮትዲቫር ተከላካዮች አስቸጋሪ እንደሚኾን ተገምቷል።

ሌላው የለሊት 6፡00 ላይ ተጠባቂው ጨዋታ ፈረንሳይ ከስዊድን የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።

በጉጉት የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ በፈረንሳይ ተጫዋቾች ድንቅ ብቃት እና በስዊድን ጠንካራ የቡድን ሥብሥብ መካከል የሚደረግ የአውሮፓውያኑ ፍልሚያ ይኾናል።

የፈረንሳዩ ኪሊያን ምባፔ በፈጣን እግሮቹ እና በግብ የማግባት ብቃቱ እንዲሁም ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ዑስማን ደምበሌ የጨዋታው ዋነኛ ልዩነት ፈጣሪ እንደሚኾኑ ይጠበቃል።

በስዊድን በኩል ቪክቶር ጂዮኬሬስ በአውሮፓ እያሳየ ባለው ድንቅ የግብ ማስቆጠር ብቃት የፈረንሳይን ተከላካዮች የሚፈትን ይኾናል።

አሌክሳንደር ኢሳክ ለፈረንሳይ ተከላካዮች ስጋት እንደሚኾን የሚጠበቅ ሌላው ተጫዋች ነው።

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ሌሊት 10:00 ላይ ሜክሲኮ ከኢኳዶር የሚገናኙ ይኾል።

አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here