ባሕር_ዳር: ሰኔ 24/2018 ዓ.ም ⚽️በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዛሬ እንግሊዝ ከዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ቤልጅየም ከሴኔጋል የሚያደርጉት ፍልሚያ 🌏በጉጉት ይጠበቃል።
ለዓለም ዋንጫ አሸናፊነት ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት መካከል የኾነችው እንግሊዝ የወቅቱን ምርጥ ቡድኗን ይዛ ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ክሮሽያ እና ፓናማን አሸንፎ፣ ከጋና ጋር አቻ በመለያየት 32ቱን መቀላቀሉ ይታወሳል።
ሃሪ ኬን፣ ሳካ፣ ራይስ፣ ቤሊንግሃም፣ ራሽፎርድ እና ሌሎች ክዋክብቶችን በሥብሥቡ የያዘው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካዊቷ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን በኮሎምቢያ ተሸንፎ፣ ኡዝባኪስታንን አሸንፎ፣ ከፖርቸጋል ጋር አቻ በመለያየት 32ቱን መቀላቀሉ ይታወሳል። ጨዋታው ምሽት 1:00 ላይ ይካሄዳል።
በሌላ መርሐ ግብር ምሽት 5:00 ላይ ቤልጄም ከ ሴኔጋል ይጫወታሉ። ምርጥ ሦሥተኛ በመኾን ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ከቤልጄም ብርቱ ፈተና ይጠብቀዋል።
በሌላ መርሐ ግብር አዘጋጇ ሀገር አሜሪካ ሌሊት 9:00 ላይ ከቦሲኒያ ጋር ትጫወታለች።
#አሚኮ_ዜና #ዓለም_ዋንጫ🌏#ስፖርት⚽️
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!።



