ብራዚል ከጃፓን እና ሞሮኮ ከኔዘርላንድስ የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው ⚽️🏆

0
63

 

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብሮች ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ፣ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

የአምስት ጊዜ የመድረኩ አሸናፊ ብራዚል ወደ 16ቱ ለመቀላቀል ከጃፓን ጋር ምሽት 2:00 ላይ የምታደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል።

ብራዚል በ7 ነጥብ ምድብ ሦስትን በበላይነት በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሲኾን ጃፓን በአንጻሩ በምድቧ ምንም ሽንፈት ሳታስተናግድ 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በሌላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምድብ አምስትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ጀርመን ምርጥ ሦስተኛ በመኾን 32ቱን ከተቀላቀለችው ፓራጓይ ጋር ትጫወታለች፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በ2002ቱ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ላይ የተገናኙ ሲኾን ጀርመን ጨዋታውን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፏ የሚታወስ ነው።

በሌላ የዛሬ መርሐ ግብር ከምድብ-ሦስት 2ኛ ደረጃን በመያዝ 32ቱን የተቀላቀለችው ሞሮኮ ከምድብ ስድስት አሸናፊዋ ኔዘርላንድስ ጋር ሌሊት 10:00 ላይ እንደሚጫወቱ ቢቢሲ ስፖርት አስነብቧል፡፡

በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ እስከ ግማሽ ፍጻሜ መጓዝ የቻለችው ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ በዚህ የዓለም ዋንጫስ ምን ያህል ርቀት ትጓዛለች የሚለው ይጠበቃል፡፡

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በሳሙኤል ጥሩነህ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here