ጎንደር: ሰኔ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የእግር ኳስ ተጫዋች የመንግሥቱ ወርቁ መታሰቢያ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በታላቁ የእግር ኳስ ተጫዋች መንግሥቱ ወርቁ ስም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራው መሰየሙ ተተኪው ትውልድ ፈለጉን ተከትሎ በእግር ኳስ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ መነሳሳትን ይፈጥራል ብለዋል።
የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታው የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን ማስተናገድ እንደሚችል ተገልፆል። ግንባታው ከከተማው የኮሪደር ልማት ጋር በቅንጅት የተሠራ ነው። ወጣቶ ጊዜያቸውን በስፖርት ስፍራ እንዲያሳልፉ ይረዳል ተብሏል።
መንግሥቱ ወርቁ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ስም ካላቸው ታሪካዊ ተጫዋቺች መካከል አንደኛው ነው።
በ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ግብ አግቢ ኾኖ ያጠናቀቀው ጎንደር ክፍለ ሀገር የተገኘ እውቅ የእግር ኳስ ተጫዎች ነው።
ይህን የሀገር ባለውለታ ያከበረችው ጎንደር ከተማ አሥተዳደር መታሰቢያው የሚኾን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ሰይማለታለች።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የከተማ አሥተዳደሩ እና የዩኒቨርሲቲው መሪዎች፣ የመንግሥቱ ወርቁን ልጅ እና ሌሎች የቅርብ ወዳጆቹ ተገኝተዋል።
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ወቅት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ አካሂደው አቻ ተለያይተዋል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



