ባሕር ዳር: ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ አራት የመጨረሻ ጨዋታ በሶፊ ስታዲየም ቱርክየን እና አሜሪካን ያገናኘው ጨዋታ በቱርክየ 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ምንም እንኳን አሜሪካ ብትሸነፍሞ ቀደም ብላ በሠበሠበችው ነጥብ የጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች። ቱርክየ ቀደም ብላ ከፉክክሩ ውጭ መኾኗ ይታወሳል።
በሌላ የዚሁ ምድብ ጨዋታ አውስትራሊያ እና ፓራጓይ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው። ይህ ውጤት ለቡድኖቹ መልካም ኾኖላቸዋል።
ጨዋታው አውስትራሊያን ወደ ቀጣይ ዙር ሲያሸጋግር ፓራጓይን ደግሞ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚያስችላትን ጥሩ ውጤት እንድታገኝ አስችሏታል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



