ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን ለማስፈረም ተስማማ!

0
55

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ የኖቲንግሃም ፎረስት የ23 ዓመቱን አማካኝ ኤሊዮት አንደርሰንን በይፋ ለመግዛት ከስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።

እንደ ቢቢሲ ስፖርት ዘገባ ከኾነ፣ የዝውውር ዋጋው ማበረታቻዎች ጋር ተዳምሮ እስከ 130 ሚሊዮን ፓውንድ ሊደርስ ይችላል ተብሏል።

ኤሊዮት አንደርሰን ወደ ኢትሃድ ለመዘዋወር ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለክለቡ ኖቲንግሃም ፎረስት በይፋ ያሳወቀ ሲኾን ክለቡም ጥያቄውን ተቀብሎታል።

ተጫዋቹ በአሁኑ ወቅት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለዓለም ዋንጫው አሜሪካ ስለሚገኝ የህክምና ምርመራውን እዛው አሜሪካ ውስጥ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በሳሙኤል ጥሩነህ (የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here