የለደን ማራቶን ከ2027 ጀምሮ በሁለት ቀናት እንዲከናወን በመላው ዓለም የሚገኙ ተሳታፊዎች ሀሳብ አቀረቡ።

0
41
ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፕላቲኒየም ደረጃ የሚሰጠው እና ከአራቱ ዋና ዋና የማራቶን ውድድሮች አንዱ የኾነው የለንደን ማራቶን በ2027 ለሁለት ቀናት እንዲደረግ ሀሳብ መቅረቡን የለንደን ማራቶን ሥራ አሥኪያጅ ሒዩ ብራሸር አስታውቀዋል።
ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በለንደን ማራቶን የሚሳተፉ ሰዎች ፍላጎት በየዓመቱ እየጨመረ መምጣት ነው ብለዋል።በዚህ ምክንያት በቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ 24/2027 ቅዳሜ እና ሚያዝያ 25/2027 እሑድ 100 ሺህ ሰዎች በማራቶኑ እንዲሳተፉ ለማድረግ የቀረበውን ሀሳብ የተቀበሉ ሲኾን ቀጣዩ ሥራቸው ድምጽ እንዲሰጥበት ማድረግ እንደኾነ ጠቁመዋል።
በለንደን ማራቶን ውድድር ላይ ለበጎ አድራጎት እና ለልዩ ልዩ ተግባራት 150 ሚሊዩን ፓውንድ እንደሚሠበሠብ የገለጹት አዘጋጆች በቀጣይ የበጎ አድራጎት ተግባራትን እናሰፋለን ብለዋል።
የለንደን ማራቶን ለሁለት ቀናት መከናወኑ ለእንግሊዝ ኢኮኖሚ የ400 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተነግሯል።
በ2027 የለደን ማራቶን በሁለት ቀን ይከናወን የሚሉ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚኾኑ ሰዎች የሰጡት ድምጽ ውጤት ሐምሌ ወር ይፉ እንደሚደረግ ተገልጿል።
በመልሰው ጥበቡ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here