🏃‍♂️🏃‍♀️የ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተወዳዳሪ አትሌቶች በባሕር ዳር!

0
31

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ነፋሻማዋ የባሕር ዳር ከተማ በማለዳው 1ኛውን የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የአትሌቶች ሩጫ ውድድር አካሂዳለች።

በዘንባባ የተዋቡ የባሕር ዳር ከተማ ጎዳናዎች ለተወዳዳሪዎች ምቹ ኾነው ታይተዋል።

ከጣና የሚነሳውን ነፋስ እየቀዘፉ፤ በዘንባባ አረንጓዴ ልማቷ ላይ፤ ባለ ግርማ ሞገሱን አዲሱ ድልድይ እያቋረጡ ውድድራቸውን አካሄደዋል።

የቱሪዝም መዳረሻዋ ባሕር ዳር ከተማ 1ኛውን የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በድምቀት አስተናግዳለች።

#አሚኮ-ዜና# ስፖርት# ባሕርዳር# አማራ ክልል#ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here