ማንቸስተር ሲቲ በርካታ ተጫዋቾችን ለዓለም ዋንጫው በማስመረጥ ቀዳሚነቱን ያዘ።

0
59

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሊጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ በቀረው የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ፣ ታላላቅ የዓለም ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ለብሔራዊ ቡድኖች በመላክ ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

እንደ ያሆ ስፖርት መረጃ የእንግሊዙ ግዙፍ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ በርካታ ተጫዋቾችን ለዓለም ዋንጫው በማስመረጥ ቀዳሚነቱን ይዟል።

ማንቸስተር ሲቲ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በ48 ሀገራት ፉክክር በሚካሄደው በዚህ የዓለም ዋንጫ ላይ 19 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚነቱን ይዟል።

ባየር ሙኒክ 18፣ አርሰናል 16፣ ፒኤስጂ15፣ ባርሴሎና 14 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ተከታዩን ቦታ ይዘዋል።

ከ6ኛ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ደግሞ የሳዑዲ ዓረቢያው አል ሂላል፣ የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ የእንግሊዞቹ ክሪስታል ፓላስ እና ማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ መካተት ችለዋል።

ይህ የተጫዋቾች ምርጫ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሁንም የዓለማችን ጠንካራው እና ኮከብ ተጫዋቾች የሚሠበሠቡበት ሊግ መኾኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

ይህ የክለቦች የተጫዋቾች ስብስብ በዓለም ዋንጫው ላይ ለሚኖረው የጨዋታ ፉክክር ትልቅ ማሳያ ኾኗል።

በምስጋናው ብርሃኔ

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here