ከአንድ ማህጸን ወጥተው ለሁለት የተለያዩ ሀገራት የሚጫወቱት ኮከቦች።

0
75

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከፈረንሳዊቷ እናት እና ከኮትዲቯሩ አባት የተወለዱት ወንድማማቾቹ የእግር ኳስ ጅማሯቸውን በፈረንሳዩ ሬን ክለብ በጋራ አድርገዋል። በሂደት ግን በክለብም ኾነ በብሔራዊ ቡድን የተለያየ መስመር ለመከተል ወስነው የኳስ ሕይወታቸውን እያስኬዱ ይገኛሉ።

ታላቅ ወንድም ጉኤላ ዱዌ በአሁኑ ወቅት ለስትራስቡርግ ክለብ ይጫወታል። በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ የአባቱን ሀገር ኮትዲቯርን መርጧል።

ታናሽ ወንድሙ ዲዚሬ ዱዌ ለፈረንሳዩ ግዙፍ ክለብ ፒኤስጂ እየተጫወተ ነው። የብሔራዊ ቡድን ምርጫው ደግሞ የእናቱ ሀገር ፈረንሳይ ናት። በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዲዲየር ዴሻምፕ ተመርጦ ፈረንሳይን ወክሎ በ2026 ዓለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋል።

እነዚህ ከአንድ ቤተሰብ የወጡ ወንድማማቾች ትናንት የተለያየ ሀገር ወክለው ተገናኝተዋል። ፈረንሳይን ከኮቲዲቯር ባገናኘው የወዳጅነት ጨዋታ ወንድማማቾቹ በተለያየ ሀገር እና መለያ ታይተዋል።

ኮትዲቯር ፈረንሳይን 2 ለ 1 ባሸነፈችበት የወዳጅነት ጨዋታ ጉኤላ ዱዌ ለሀገሩ ኮቲዲቯር ግብ አስቆጥሯል።

ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚጀምረው የዓለም ዋንጫ ላይ እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች በተለያየ የሀገራት ማሊያ እንደሚጫወቱ ያሁ ስፖርት ዘግቧል።

በምስጋናው ብርሃኔ

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_እግር_ኳስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here