ሊቨርፑል አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ለመሾም ከስምምነት ላይ ደረሰ።

0
26

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከቀናት በፊት አሠልጣኝ አርኔ ስሎትን ያሰናበተው ሊቨርፑል ስፔናዊውን አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ አዲሱ የክለቡ ዋና አሠልጣኝ አድርጎ ለመሾም ስምምነት ላይ መድረሱ ተዘግቧል።

የቀድሞው የቦርንማውዝ አሠልጣኝ በመርሲሳይዱ ክለብ ለሦሥት ዓመታት የሚያቆያቸውን ውል ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመጀመሪያው የሊቨርፑል አሠልጣኝነት ዘመናቸው የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ዋንጫን ያሸነፉት አሠልጣኝ አርኔ ስሎት በሁለተኛው የውድድር ዘመን ግን ሊቨርፑልን በጥንካሬው ማስቀጠል አልቻሉም። ክለቡም ወደ ቀደመ ጥንካሬው ለመመለስ አሠልጣኙን አሠናብቷቸዋል።

የእርሳቸውን ኀላፊነት ለመረከብ አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተዘግቧል።

በቦርንማውዝ አሠልጣኝነት ጊዜያቸው የተደነቁት አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ሊቨርፑል ትክክለኛ ምርጫ እንደኾኑ ያመነባቸው እርሳቸውን መኾኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

አሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ በቦርንማውዝ ቤት ታላላቅ ክለቦችን ሁሉ የሚያሸንፍ ጠንካራ ስብስብ መገንባት ችለዋል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት #እግር_ኳስ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here