ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፍጻሜውን ባገኘው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ የተሳተፉ ታላላቅ ክለቦች እንደየደረጃቸው እና ካስመዘገቡት ውጤት ተነስተው የሚያገኙት የገንዘብ መጠን ይፋ ኾኗል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር (ዩ ኢ ኤፍ ኤ) ለክለቦች የሚሰጠውን የሽልማት ገንዘብ የሚወሰነው በሦሥት ዋና ዋና መስፈርቶች ሲኾን እነሱም በውድድሩ ላይ እስከ የትኛው ደረጃ ድረስ እንደተጓዙ ክለቦቹ ባላቸው የ10 ዓመት የአውሮፓ ውድድሮች ደረጃ እና ከቴሌቪዥን ሥርጭት መብት ሽያጭ በሚገኝ ገቢ ላይ ተመስርቶ ነው።
ክለቦቹ ከውድድሩ ያገኙት የገንዘብ መጠን በደረጃ ሲቀመጥም
ፒኤስጂ 127 ሚሊዮን ፓውንድ፤ አርሰናል 124 ነጥብ 73 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ባየር ሙኒክ 110 ነጥብ 84 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ሊቨርፑል 95 ነጥብ 35 ሚሊዮን ፓውንድ፤ አትሌቲኮ ማድሪድ 90 ነጥብ 76 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ሪያል ማድሪድ 90 ነጥብ 17 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ባርሴሎና 86 ነጥብ 58 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ማንቸስተር ሲቲ 84 ነጥብ 49 ሚሊዮን ፓውንድ፤ ቼልሲ 80 ነጥብ 210 ሚሊዮን ፓውንድ እና ቶተንሀም ሆትስፐር 74 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፓውንድ ኾነው ተደልድለዋል።
እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ ይህ እጅግ ከፍተኛ የኾነ የገንዘብ ክፍያ ክለቦች በቀጣዩ የክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ኾነው እንዲቀርቡ እና የፋይናንስ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል ሲል አስነብቧል።
በምስጋናው ብርሃኔ
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰአሚኮ_ዜናብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



