አርኔ ስሎት በቀጣይ የውድድር ዘመን በሊቨርፑል እንደሚቆዩ አረጋገጡ።

0
17

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣዩ የውድድር ዘመን በክለቡ የመቆየታቸው ጉዳይ የተረጋገጠ መኾኑን ገልጸዋል። እንደ ስካይ ስፖርት ዘገባ አሠልጣኙ ከክለቡ መሪዎች ጋር ስለ አዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር ንግግር እያደረጉ መኾኑም አስነብቧል። በቀጣይ የውድድር ዘመን የሊቨርፑል አሠልጣኝ ኾኜ እንደምቀጥል ለማመን ሙሉ ምክንያት አለኝ ብለዋል አሠልጣኙ።

ከክለቡ ጋር የውል ስምምነት እንዳላቸው እና እየተደረጉ ያሉ ንግግሮችም በቆይታቸው ላይ ግልጽ የኾነ መግባባት መኖሩን እንደሚያሳይ አስታውቀዋል።

ይህም በቅርቡ ከአሠልጣኙ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ጋር ተያይዞ ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ኾኗል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here