ሉዊስ ኤንሪኬ ፒኤስጂን ለተከታታይ ሦስት ዓመታት የፈረንሳይ ሊግ ሻምፒዮን አደረጉ።

0
3
ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ስፔናዊው አሠልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የፓሪሱን ክለብ ፒኤስጂን ከተረከቡ ወዲህ፣ የዘንድሮን ጨምሮ ለሦሥት ተከታታይ የውድድር ዓመታት የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችለዋል። በዚህም ፒኤስጂ በታሪኩ 14ኛውን የሊግ ዋንጫ በእጁ አስገብቷል።
ኤንሪኬ በሊግ ውድድር ብቻ ሳይኾን፣ የክለቡን የዘመናት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሕልምም እውን ያደረጉ አሠልጣኝ ናቸው። ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የ2024/25 የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያሳካው በእሳቸው መሪነት ሲኾን፤ ዘንድሮም ለአንድ ተጫዋች ያልተገዛ ጠንካራ ሥብሥብ በመገንባት ቡድኑን ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት ለሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ አድርሰዋል።
በዘንድሮው የአውሮፓ መድረክ 44 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚ የኾነው የኤንሪኬ ቡድን፣ በፍጻሜው ከአርሰናል ጋር ይጋጠማል።
ጨዋታው ግንቦት 22/2018 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም የሚካሄድ ይኾናል። ኤንሪኬ ከዚህ ቀደም ከባርሴሎና ጋር በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገባቸው እና የስፔን ብሔራዊ ቡድንም መምራታቸው ይታወሳል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here