ጆዜ ሞሪኒሆ ወደ ሪያል ማድሪድ ይመለሱ ይኾን?

0
7

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ የጆዜ ሞሪኒሆ ወደ ሪያል ማድሪድ መመለስን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

የቀድሞው ሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ጆዜ ሞሪኒሆ ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው ቢመለሱ ጥሩ ሥራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል። ሞሪኒሆ በሠሩባቸው ክለቦች ሁሉ ስኬታማ እንደነበሩ አንስተዋል። ወደ ማድሪድ ቢመለሱም “ድንቅ ሥራ” የመሥራት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

ጆዜ ሞሪኒሆ ከዚህ ቀደም ከ2010 እስከ 2013 ባሉት ዓመታት ሪያል ማድሪድን በዋና አሠልጣኝነት መርተዋል። በቆይታቸውም ክለቡን ለላሊጋ፣ ለኮፓ ዴል ሬይ እና ለስፔን ሱፐር ካፕ ድሎች አብቅተዋል።

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ ሞሪኒሆን ለመሾም እየሠራ እንደኾነ ተገልጿል። የማድሪድን ቤት የሚያውቁት አሠልጣኙ በመልበሻ ክፍሉ ውስጥ ያለውን የተጫዋቾች አለመግባባት እንደሚያርቁ ይጠበቃል።

የማድሪዱ አለቃ ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሞሪኒሆ ወደ ማድሪድ ሊመለሱ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸው ፋብሪዚዮ ሮማኖ ጽፏል። የማድሪዱ ፕሬዝዳንት “ሆዜ ሞሪንሆ ከእኛ ጋር በነበረበት ወቅት የቡድናችንን ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ከዚያ በኋላ ባሉት 10 ዓመታት ውስጥ 6 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችለናል” ማለታቸውን ዘግቧል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here