በማድሪድ ቤት እየተተቸ ያለው ኪሊያን ሜባፔ

0
66
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ሜባፔ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ ክለቡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ትልቅ ዋንጫ ማግኘት አልቻለም። ይሄን ተከትሎ ደጋፊዎች ተጫዋቹ እንዲለቅ ፊርማ እያሠባሠቡ ይገኛሉ።
ሜባፔ በግሉ በሁለቱም የውድድር ዓመታት የላሊጋው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መኾን ቢችልም እሱ ባለባቸው ጨዋታዎች ላይ የቡድኑ የማሸነፍ ምጣኔ ዝቅተኛ መኾኑ ደጋፊዎችን አስቆጥቷል።
በተለይም ፒ ኤስ ጂን በለቀቀበት ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካቱ እና ማድሪድ ዘንድሮ በሩብ ፍጻሜ መሰናበቱ ለተቃውሞው መባባስ ምክንያት ኾኗል።
ምንም እንኳን የቪኒሺየስ እና ቤሊንግሃም ብቃት መቀነስ፣ የተከላካይ ክፍሉ ጉዳት ለውድቀቱ ተጠቃሽ ቢኾኑም ደጋፊዎቹ ግን ውድቀቱን ከሜባፔ መኖር ጋር እያያያዙት ይገኛሉ።
ክለቡ በተጫዋቹ ላይ ዕምነት እንዳለው ቢገልጽም በመጭው እሁድ ከባርሴሎና ጋር በሚደረገው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ በፊት በቡድኑ መልበሻ ክፍል ውስጥ አለመረጋጋት መፈጠሩን ቢቢሲ እና ስፖርት ዘግበዋል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

See less

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here