የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

0
73
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚዎች ዛሬ ይለያሉ።
ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቀጥሎ ትልቅ ግምት የሚሰጠው የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ።
ዛሬ ከሚደረጉ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች መካከል የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ክለቦችን አስቶንቪላን ከኖቲንግሃም ፎረስት ያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በኖቲንግሃም ፎረስት ሜዳ በሲቲ ግራውንድ 1ለ0 የተሸነፈው አስቶንቪላ በዛሬው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሶ ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
በአሠልጣኝነት ዘመናቸው አራት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፉት የአስቶንቪላው አሠልጣኝ ኡናይ ኢምሬ አስቶንቪላንም የዋንጫ ባለቤት ማድረግ ይችሉ ይኾን ? የሚለው ይጠበቃል።
አስቶንቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያሸንፋል ተብሎ ቅድመ ግምት ከተሰጣቸው ክለቦች መካከል አንደኛው ነው። አሠልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ከአስቶንቪላ ጋር የዋንጫ ባለቤት መኾን ከቻሉ በአሠልጣኝነት ዘመናቸው አምስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ይኖራቸዋል።
አሠልጣኝ ኡናይ ኢምሬ አስቶንቪላ ዋንጫውን ባያሳካም እንደ ውድቀት ሊቆጠር አይችልም ማለታቸው ኢኤስፒኤን ዘግቧል።
በአሠልጣኝ ሺቶር ፔሬራ ሥር በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስትም ብርቱ ተፎካካሪ እንደሚኾን ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ በአስቶንቪላ ሜዳ በቪላ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።
በሌላ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፍራይበርግ ከ ስፖርቲንግ ብራጋ ለፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታል። በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ስፖርቲንግ ብራጋ ፍራይበርግን 2ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል። ጨዋታውም ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል።
በታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

See less

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here