ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለምን ትኩረት የሳበው ጨዋታ በአልያንዝ አሬና ምሽት 4:00 ላይ ይከናወናል።
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ባየርን ሙኒክ በሜዳው አልያንዝ አሬና ፓሪሰን ዠርሜን ምሽት ያስተናግዳል፡፡
በፓሪስ ፓርክ ደ ፕራንስ የተከናወነው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ለዕይታ ማራኪ ኾኖ ዘጠኝ ግቦች ተቆጥረውበት ፒ ኤስ ጂ 5ለ4 ማሸነፉ ይታወሳል።
ባየርን ሙኒክ እና ፒ ኤስ ጂ በቻምፒዮንስ ሊጉ 16 ጊዜ ተገናኝተው ሙኒክ ዘጠኙን በማሸነፍ የበላይነቱን ይወስዳል፡፡ ፒ ኤስ ጂ ሰባት ድሎችን አስመዝግቧል፡፡
ባየርን ሙኒክ ውጤቱን ገልብጦ ወደ ፍጻሜው ያመራል ወይስ ፒ ኤስ ጂ ውጤቱን አስጠብቆ ይወጣል የሚለው ጉዳይ የዛሬውን ጨዋታ በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓል።
ሃሪኬን፣ ሊውስ ዲያዝ እና ማይክል ኦሊሴ የባየር ሙኒክን የፊት መሥመር በአስደናቂ ብቃት ይመሩታል።
በፒ ኤስ ጂ በኩል ደግሞ ኡስማን ዴምቤሌ፣ ክቪቻህ ክቫራስኬሊያ እና ዴዝሪ ዱዌ የሙኒክን ተከላካዮች የሚፈትኑ ይኾናል።
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



