ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለ ኢየሱስ ባዘዘው (ዶ.ር) ከእግር ኳስ ዳኝነት ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።

0
14
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለ ኢየሱስ ባዘዘው (ዶ.ር) ከእግር ኳስ ዳኝነት ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
25 ዓመታትን በእግር ኳስ ዳኝነት ያሳለፉት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለ ኢየሱስ ባዘዘው (ዶ.ር) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላቅ ያለ አበርክቶ አላቸው። ሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ የዓመቱ ምስጉን ዳኛ ክብርን በማግኘት እስከ አሁን ብቸኛው ናቸው።
ከ25 ዓመታት የእግር ኳስ የዳኝነት ቆይታ በኋላ ዳኝነት በቃኝ ብለው ፊሽካ መስቀላቸውን ለአሚኮ አስታውቀዋል። በቀጣይ ከዳኝነት ባለፈ በክልሉም ይሁን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ በሙያቸው ለማገልገል ፈቃደኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ባለፋት 25 ዓመታት እዚህ እንዲደርሱ ከጎናቸው የነበሩትን ሁሉ አመስግነዋል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ኋይለ ኢየሱስ ባዘዘው (ዶ.ር) በስፖርት ሳይንስ የሦሥተኛ ዲግሪ አላቸው። በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ ኾነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ:- መልሰው ጥበቡ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here