አዲስ አበባ: ሚያዚያ 12/2018 (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 29ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤው ከሚወያይባቸው ጉዳዮች መካከል፦

የ28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤን ማፅደቅ፣

የ2017 በጀት አመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

የውጭ ኦዲተርን መሰየም እና የ2017 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲት ሪፖርት በማዳመጥ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

ተቋማዊ አሠራር (ሪፎርም) ሰነድ እና የሰው ኀይል መዋቅራዊ ጥናት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

የተሻሻለውን የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ አይቶ ማጽደቅ፣

የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

የተሻሻለውን የፌዴሬሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አሥተዳደር መመሪያን ማጽደቅ ይገኙበታል።