በስፖርታዊ ውድድሮች አንድነትን ለመፍጠር እየተሠራ ነው።

0
34

 

ከሚሴ: ሚያዚያ 11/2018 (አሚኮ) በቻዴት ኢትዮጵያ አዘጋጅነት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎችን ያሳተፈ የእግር ኳስ ውድድር ተካሂዶ ተጠናቅቋል።

ውድድሩ አጎራባች ወረዳዎቹ ያላቸውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ስፖርታዊ ውድድሩ ወንድማማችነትን ለማጠናከር አስተዋጽኦ ያለው መኾኑን ገልጸው የተጀመረው የሰላም እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ጀማል ሀሰን የሁለቱን አጎራባች ሕዝቦች ወንድማማችነት ለማጠናከር የስፖርት ውድድሮች እና የባሕል ፌስቲቫሎችን ለማዘጋጀት በትኩረት እንደሚሠራ አብራርተዋል።

ቻዴት ኢትዮጵያ ለስፖርተኞች ላደረገው የትጥቅ ድጋፍ አመሥግነው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የስፖርት ቡድን መሪ ፀጋዬ በቀለ ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከቻዴት ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሁለቱ ዞኖች የተለያዩ የሰላም ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸው በአራት ወረዳዎች የወጣቶችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር ስፖርታዊ ውድድሮችን በማድረግ የበለጠ አንድነትን ለመፍጠር እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የተጀመረውን የእርስ በእርስ ግንኙነት በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የቻዴት ኢትዮጵያ አስተባባሪ አስቻለው ታደሰ በበኩላቸው ቻዴት ኢትዮጵያ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በቀጣይም በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር ስፖርታዊ ውድድሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በውድድሩ የተሳተፉ የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አጎራባች ወረዳዎች ስፖርተኞች እንደገለጹት ስፖርታዊ ውድድሮች ከጨዋታው ባሻገር የእርስ በእርስ ግንኙነትን ለማጠናከር እና ሰላምን ለማጽናት ትልቅ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

አንዱ የሌላውን ባሕል እና እሴት ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸው በዚህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።

ዛሬ በተካሄደው ውድድር ከሚሴ ከተማ ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ለፍፃሜ ባደረጉት ጨዋታ ከሚሴ ከተማ ሁለት ለአንድ በኾነ ውጤት አሸናፊ ኾኗል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

#እግር_ኳስ #ስፖርት #መዝናኛ #ወጣቶች #አሚኮ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here