አጼዎቹ ከወላይታ ዲቻ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም!

0
30

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ዛሬም ሲቀጥል አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ ምሽት 12፡00 ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ከሊጉ የፊት መስመር አጋፋሪዎች መካከል ኾኖ ጥሩ ተፎካካሪ ለመኾን እየጣረ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በ39 ነጥብ እና በ3 የግብ ክፍያ አምስተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።

በዛሬው ጨዋታም ተጋጣሚውን አሸንፎ ደረጃውን ለማሻሻል እና ጥሩ ተፎካካሪ ለመኾን ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።

ባለፈው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን 1ለ0 በማሸነፍ ጥሩ የሥነልቦና ግንባታ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ዛሬም የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ነው የሚጠበቀው።

ተጋጣሚው ወላይታ ዲቻ በሊጉ በ31 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መኾኑ እና ባለፈው ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1ለ0 በማሸነፍ ጥሩ ቁመና ላይ ያለ በመኾኑ ለፋሲል ቀላል አይኾንለትም።

ሌሎች የሊጉ ጨዋታዎችም ዛሬ ሲደረጉ አዲስ አበባ ላይ በአበበ ቢቄላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 7፡00 ላይ ይጫወታሉ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና እና አዲስ አበባ ላይ በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ 10፡00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here