ተጠባቂው የባየርን ሙኒክ እና የሪያል ማድሪድ ጨዋታ

0
39
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ባየርን ሙኒክ በሜዳው ሪያል ማድሪድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ደግሞ ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁት ነው።
ሁለቱ ክለቦች በሳንቲያጎ ቤርናባው ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ባየርን ሙኒክ 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ባለሜዳው ቡድን ባየር ሙኒክ ውጤቱን አስጠብቆ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ሪያል ማድሪድ ደግሞ ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ ሰዓት አርሰናል በሜዳው ኤምሬትስ የፖርቹጋሉን ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ያስተናግዳል፡፡
አርሰናል ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ያደረገውን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በካይ ሀቨርትዝ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል።
አርሰናል አሁን ላይ በሻምፒዮንስ ሊግ እየተሳተፈ የሚገኝ ብቸኛው የእንግሊዝ ክለብ ነው። ሁለቱም ጨዋታዎች ምሽት 4:00 ይካሄዳሉ።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here